የኬሬን ሃሀዳሻ ድርጅት ዓላማና ተግባር

"ሃኬሬን ሃሀዳሻ ለይሥራኤል ድርጅት" ለጠቅላለዉ የእሥራኤል ዜጎች ዲሞክራሲን፤ ፍትህንና እኩልነትን ለማስፈን የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነዉ። በእሥራኤል አገር መስራቾች እራይ መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ማህራዊና ፓለቲካዊ መስኮች በእኩልነት የተመሰረተ ህይወቱን እንዲመራ ብሎም የሐይማኖት፤ የዘርና ጾታ ልዩነት የሌለበት ህይወቱን መምራት ይችላል ብለን እናምናለን።

በእሥራኤል አገር ዜጎችን ኖሮ ለማሻሻል በተለይ ደካማ የህብረተሰብ መደብ የሚወክሉ ዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ምህበራዊ ድርጅቶችን አቋቁመዉ የሚንቀሳቀሱትን ዜጎች ለማጠናከር ድጋፍ እናደርግላቸዋለን። የኬሬን ሀዳሻ ድርጅት በእሥራኤል ህብረተሰብ ደካማ የህብረሰብ መደቦችን ህይወት ለማሻሻል ያለዉን የሰዉና ማቴሪያል ሁሉ ይሰዋል። ድርጅቱ ከተመሰረተበት ቀን አንስቶ እስካሁን ከ850 በላይ ድረጅቶች ከ250 ሚሊዩን ዶላር በላይ እርዳታ ለግሷል። የገንዘብ እርዳታ የተቀበሉ ድርጅቶች የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዉ ለማሻሻል በፊልድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ፤ በሐብታሞችና በድሆች መካካል ያለዉን የገቢ ምንጭ ልዩነት ለመቀነስ የሚታገሉ ድርጅቶች፤ ለሴቶች እኩልነት የሚታገሉ ድርጅቶች፤ ነጻነት የሰፈነበት የፕሎራሊዝም ይሁዳዉያን ሐይማኖት መርሆ የሚከተሉ ድርጅቶች፤ ለሐይማኖት ነጻነት ታጋይ ድርጅቶች፤ ለሰዉ ልጆች መብት ተሟጋች ድርጅቶች፤ አዲስ ገቢዎችን የሚረዱ ድርጅትና በአካባቢ ፍትህ እንዲሰፍን የሚተጋሉ ድርጅቶች ናቸዉ።

ሃኬሬን ሃሀዳሻ ለይሥራኤል ድርጅት የተሻለ ማህበራዊ ለዉጥ እንዲሆን በተቀዳሚነት የሚያከናዉናቸዉን  ሥራዎች የሚያስፈፅመዉ ሻቲል በተባለዉ ( ማህብራዊ ለዉጥ ለማምጣት) የምክር አገልግሎት በሚለግሰዉ የኬረን ሃዳሻ አካል በሆነዉ አማካኝነት ሲሆን የደካማ የዜጎችን የረጅም ጊዜ ማህበራዊ ኖሮ ለማሻሻል ድርጅት አቋቁመዉ በፊልድ ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አስፈላጊዉን እርዳታ ይለግሳል ።

ሻቲል ድርጅት በጂኦገራፊዊና አቀማመጥ እርቆ ከሚገኝ ዝቅተኛ የገቢ ምንጫ የሚያገኝ ህዝብ ከሚኖርበት ቦታ በመድረስ ድርጅቶችን በማቋቋም ማህበራዊ ህይወቱን ያጠናክራል።  የሻቲል ድርጅት በሚያደረገዉ እንቅስቃሴ ዜጎች በመንግስታዊ ጉዳዩች ጣልቃ እንዲገቡ የሞራል ድጋፍ በማድረግና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ፍትህ እንዲሰፍን ለሚያካሃዱት ትግል ድጋፍ በማድረግ  የእሥራኤልን ዲሞክራሲዊ ሥርዓት ያጎለብታል። የሻቲል ድርጅት በአመላዉ አገሪቱ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ አማካኝነት በእየ ዓመቱ የተሻለ ማህበራዊ ለዉጥ ለማምጣት ለሚታገሉ ከ1000 በላይ ለሆኑ ድርጅቶች ለመቋቋም በሂደት ላይ ከሚገኙበት ስዓት አንስቶ ከተቋቋሙ በኋላ በሚያካሃዱት እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርግላቸዋል።